የሳዑዲ ዓረቢያ ሲቪል መከላከያ ጠቅላይ ዳይሬክቶሬት በኤሌክትሪክ ንክኪ (ሾርት ሰርኪት) የሚነሳ የእሳት አደጋን ለመቀነስ በቤቶችና በተቋማት የሚገኙ የኤሌክትሪክ ሥርዓቶች በየጊዜው እንዲጠገኑ ጥሪ አቅርቧል።
ዳይሬክቶሬቱ እንደገለጸው ለእንደዚህ ዓይነቱ እሳት ዋና ዋናዎቹ ሶስት ምክንያቶች ትክክል ያልሆኑ የኤሌክትሪክ ግንኙነቶች፣ በሶኬቶች ላይ ከአቅማቸው በላይ ጭነት መጫንና አውቶማቲክ የወረዳ መቆራረጫዎችን (ሰርኪት ብሬከር) አለመግጠም ናቸው።
ሲቪል መከላከያው በመገናኛ ብዙኃንና በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጫቸውን የደኅንነት መመሪያዎች እንዲከበሩ ጠይቋል። ድንገተኛ አደጋ ሲያጋጥም በመካ፣ በመዲና፣ በሪያድና በምሥራቃዊ ክልል 911፣ በቀሪዎቹ የመንግሥቱ ክልሎች ደግሞ 998 በመደወል እርዳታ መጠየቅ ይቻላል።
